ይህንን ዝግጅት እንዲቻል ላደረጉት ስፖንሰሮቻችን እና በጎ ፈቃደኞች በሙሉ እናመሰግናለን።
🎬 የሁለት ደቂቃ መክፈቻ ቪዲዮን ይመልከቱ።
📍
ቅዳሜ፣ መስከረም 23፣ 2023፣ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ2023 የቢቂላ ሽልማት አከባበር እና እራት በቶሮንቶ በሚገኘው ዳንኤልስ ስፔክትረም አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበርው በላቀ ዝግጅት ተመልሷል።
የተከበሩ ዶ/ር ጂን ኦግስቲን፣ ታዋቂዋ የካናዳ የቀድሞ ፓርላማ አባል፣ በክብር እንግዳነት በመገኘት ሁሉንም ሰው የማረከ ንግግር አድርገዋል። ታዋቂው ደራሲ እና የአፍሪካ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተንታኝ ዶ/ር ሎረንስ ፍሪማን የወቅቱን የአፍሪካና የዓለማችንን ሁኔታ ግንዛቤ አካፍለዋል።
በዚህ ደማቅ ምሽት የመራችው በሲፒ24 መልሕቅና ዘጋቢ ኤደን ደበበ ዝግጅቱን በመልካም አንደበተ ርቱዕነት ነበር የመራችው። የኢትዮጵያ አንፀባራቂ ኮከብ ሽልማት ለሟቹ ለተከበሩ አቶ ከተማ ይፍሩ ላደረጉት ትልቅ አስተዋፅዖ ተበርክቷል፣ ልጃቸው መኮንን ከተማ ይፍሩ በመላው ቤተሰብ ስም ተቀብሏል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ላሳዩት የላቀ ሚናና የህይወት ዘመን ሽልማት ተሸላሚ የሆኑት አቶ ግርማ ዋቄ ሲሆኑ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ጣሰው: የኢትዮጵያ አየር መንገድን፤ ዓለምአቀፍ የአየር መንገድ ልህቀት ተምሳሌትነት ሽልማት ተቀብለዋል።
የአካዳሚክ ልህቀት ሽልማት ተሸላሚዎችና የ2023 የቢቂላ ስኮላርሺፕ ተሸላሚ አዳም አወቀ፣ ዶ/ር መክሊትና ሊሊያን አበበ ከፍተኛ የአካዳሚክ ችሎታ ስላሳዩ ሸልማትና አድናቆትን አግኝተዋል።
በመቀጠል በሙያቸዉ ከፍተኛ ልህቀት ያሳዩት፣ ፍሰሃ አጥላው፣ ዶ/ር ብርሃኑ ቡልቻ፣ ጆሞ ታሪኩና ቤተልሄም ደሴን ያካተተ ሲሆን ሁሉም የፕሮፌሽናል ልህቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የኃይሌ-መናስ አካዳሚ የልህቀት ትምህርት ተቋም ሽልማት ሲወስድ፤ መስራች ርብቃ ኃይሌ ሽልማቱን ተቀብላለች።
እሸቱ መለሰ፣ ሊበን ገብረሚካኤልና ፒፕል ቱ ፒፕል ካናዳ ለላቀ የማህበረሰብ አገልግሎት ዕውቅና የተዘጋጀውን ሽልማት ተቀብለዋል።
ምሽቱ ደማቅ፣ አስደሳችና በጭብጨባ የታጀበ ሲሆን፣ የዝግጅቱ ድባብ በአስደሳች እራት፣ በጃዝ ሙዚቃ፣ የበር ላይ ሽልማቶች የተካተቱ ሲሆን፣ ይህ ከኮቪድ ዘመን ተግዳሮቶች በኋላ በደመቀ ሁኔታ መመለሱን የሚያመለክትና፣ አዳራሹን የሞሉት ታዳሚዎች የአንድነትና የህብረት ምስክርነት የታየበት ነበር።
ስለ ቢቂላ ሽልማት ድርጅት ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት እና ከዚህ ቀደም የተከበሩ የተሸላሚዎችን ሙሉ ዝርዝር ለማየት፣ www.bikilaaward.org ይጎብኙ።
እውቅና ለማግኘት አትስሩ፣ ግን እውቅና የሚገባውን ስራ ስሩ።" - ኤች. ጃክሰን ብራውን፣ ጁኒየር
Credits:
በሊዮን አማኑኤል፣ ገዛኸኝ አስፋው እና ኢትዮፊደል የተነሱ ምስሎች። በበሀይሉ አጥናፉ ዳይሬክት የተደረገ ቪዲዮ፣ መዝጊያ ቪዲዮ፣ ስክሪፕት እና ድምጽ አስረስ አሰፋ፣ በወንድወሰን ገሠሠ የተቀናበረ።